One of the most common questions we get is about alcohol. Some Dalu students have noticed that when they are trying to do business in China or with Chinese people, a lot of drinking is involved, especially during a business dinner or banquet.

This culture is present in many other Asian countries as well. The purpose is for the business people to relax and get to know each other. Here is what you need to know.

  1. Bai jiu (白酒) : This Chinese liquor is usually served during dinners and banquets. It is clear in color (like water) and is extremely strong. Drink in moderation.
  2. Gan Bei (干杯)The phrase “gan bei” means “dry cup.” If someone says “gan bei!” to you that means that you two have to drink the whole cup. It is the same as saying “bottoms up.”
  3. Clinking glasses: In many cultures, we say “cheers” and clink our glasses. In China, if someone you are clinking your glass with is older or higher in position, you should lower your glass to him/her. It is a sign of respect. See the picture below.
  4. What if you do not want to drink?: In order to not embarrass your Chinese host, you will have to give a very good excuse. Religion and health reasons are usually accepted. You could also tell your Chinese host that you are planning to have a baby. This “baby” excuse works for both men and women.

በንግድ አካባቢ ያሉ ኢትዮጵያውያን ብዙ ጊዜ ስለ ቻይና እና የመጠጥ ባህላቸው ይጠይቁናል። ቻይና ሀገር ውስጥ በንግድ ወይም በቢዝነስ የእራት ግብዣ ላይ ብዙ መጠጥ መጠጣት የተለመደ ነው።

ይህ ባህል ከቻይናም በላይ በተለያዩ የእስያ ሀገሮች የተስፋፋ ነው። የዚህ ባህል ዋና አላማ ሰዎች ዘና ብለው ቢዝነስ ውስጥ እንዲገቡ እና ፈታ ብለው እንዲተዋወቁ ነው። ማወቅ ያለብዎትን ነገሮች ከስር ዘርዝሬያለሁ።

  1. ባይ ጂዮ (白酒):ይህ “ባይ ጂዮ” የተባለው መጠጥ ብዙ ጊዜ የሚቀርብ እና በቻይና የእራት ግብዣዎች ላይ የማይቀር ነው። ቀለሙ ውሃማ ሲሆን በጣም ሀይለኛ እና ቶሎም ወደ ስካር የሚዳርግ ነው። ይህን ሲጠጡ ጠንቀቅ ይበሉ።
  2. ጋን ቤ (干杯): በቻይንኛ “ጋን ቤ” ማለት “ደረቅ ኩባያ” እንደማለት ነው። አንድ ሰው “ጋን ቤ!” ሲልዎት ሁለታችሁም ብርጭቆአችሁ ውስጥ ያለውን መጠጥ መጨረስ ይኖርባችኋል። ብርጭቆው ደረቅ እሲኪሆን ወይም ውስጡ ምንም ፈሳሽ እንዳይኖር አድርጋችሁ ጠጡ እንደማለት ነው።
  3. ብርጭቆን “ቺርስ” ማስደረግ   በአማርኛ ቋንቋ ከአብሮን የሚጠጣ ሰው ጋራ “ለጤናችን” ብለን ብርጭቆዎቻችንን ነካ እናደርጋለን። የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ደግሞ “ቺርስ” ይላሉ። በቻይና ሀገር በእድሜ ወይም በስራ ዘርፍ ከእርስዎ በላይ ያለ ሰው ጋራ “ቺርስ” ሲሉ ብርጭቆዎን ዝቅ ማድረግ እንዳይረሱ። ብርጭቆን ዝቅ ማድረግ አክብሮትን ይገልፃል።ይህን የበለጠ ለመረዳት ከስር ያለውን ፎቶ ይመልከቱ።

4. መጠጣት ባይፈልጉስ? መጠጣጥ የማይፈልጉ ከሆነ ጥሩ ምክንያት መስጠት ይኖርብዎታል። አለዚያ ቻይናዊ ጋባዥዎን ሊያስቀይሙ ይችላሉ። ሀይማንዎትዎ የማይፈቅድ መሆኑን ወይም የጤና ችግር እንዳለብዎት ቢገልፁ ተቀባይነት በቀላሉ ሊያገኙ ይችላሉ። በተጨማሪም ልጅ በቅርቡ የማርገዝ ሀሳብ እንዳልዎት መንገር ይችላሉ። ወንድ ከሆኑ ባለቤትዎ እና እርስዎ ልጅ የመውለድ ሀሳብ እንዳልዎት ከተናገሩ አጥጋቢ ምክንያት ሰጡ ማለት ነው!